መረጃየኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ፣ በግል የጤና ተቋማትና መድኃኒት መደብሮች ውስጥ የሚቀጠሩ አዲስ ባለሙያዎች ከዚህ በኋላ የቅጥር …

- Advertisement -
Sidebar AD
መረጃ‼️
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ፣ በግል የጤና ተቋማትና መድኃኒት መደብሮች ውስጥ የሚቀጠሩ አዲስ ባለሙያዎች ከዚህ በኋላ የቅጥር ውል ሲፈጽሙ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት የጤና መዋቅሮች እውቅና እንዲኾን አዘዘ።
የግል የጤና ተቋማት አዲስ የሚቀጥሯቸው ባለሙያዎች ሥራ ከጀመሩበት ቀን አንስቶ ሙሉ መረጃቸውን ለክልሉ ጤና ቢሮ መላክ እንዳለባቸውም መታዘዛቸውንም ቢሮው በክልሉ ለሚገኙ 21 የዞን የጤና መምሪያዎች ከጻፈው ደብዳቤ ላይ ዋዜማ ተመልክታለች።
ቢሮው፣ በግል የጤና ተቋማትና መድኃኒት መደብሮች ውስጥ ለሚቀጠሩ አዲስ ባለሙያዎች የሚከፈላቸው ደመወዝ በመንግሥት የጤና ተቋማት ውስጥ ለሚሠሩ ባለሙያዎች ከሚከፈላቸው ደመወዝ ማነስ እንደሌለበት ጭምር ትዕዛዝ አስተላልፏል።
በደብዳቤው ላይ የተጠቀሱትን ትዕዛዞች ተፈጻሚ በማያደርጉ የግል የጤና ተቋማት ላይ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ቢሮው አስጠንቋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: