ኢትዮጵያ ይፋዊ አበዳሪዎች ኮሚቴ (OCC) ውጭ ላሉ አካላት የተሻለ የዕዳ ክፍያ ሁኔታ እንደማታቀርብ አስታወቀች
የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ ከሁሉም የውጭ አበዳሪዎች ጋር የሚደረገው የዕዳ ሽግሽግ በይፋዊ አበዳሪዎች ኮሚቴ (OCC) ማዕቀፍ ስር “የእኩል መስተንግዶ” መርህን የተከተለ እንደሚሆን ገለፀ።
መንግስት ከዚህ ማዕቀፍ ውጭ ላሉ የውጭ አበዳሪዎች የተሻለ የክፍያ ሁኔታ ላለማቅረብ ቃል ገብቷል።
በዚህም መሰረት፣ ከሌሎች ወገኖች ጋር ተመሳሳይና እኩል የሆነ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ እስኪደረስ ድረስ መንግስት ለእነዚህ አበዳሪዎች የሚከፈለውን ዕዳ ሳይከፍል በጊዜያዊነት እንደሚቆይ አስታውቋል።
ይህ አሰራር የዕዳ እፎይታ ሸክሙ በሁሉም አበዳሪዎች ላይ በእኩልነት እንዲያርፍ ለማድረግ የታለመ ነው።
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2021 በጂ20 ማዕቀፍ ስር የዕዳ ማሻሻያ ጥያቄ ካቀረበች ጀምሮ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በኢኮኖሚ ጫናዎች ምክንያት የዕዳ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ከሁለትዮሽ እና ከግል አበዳሪዎች ጋር የምታደርገውን ድርድር በቅንነት እንደምትቀጥል ገልጻለች።
@Seledadotio

No comments yet.