የኢትዮጵያ መድን ክለብ ወጣቱን የግራ መስመር ተከላካይ ከስብስብ ውጪ አደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር የኢትዮጵያ መድን ቡድን በሲዳማ ቡና በፍጹም ቅጣት ምት በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ በ33ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ሲወጣ ማልያውን አውልቆ በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ ፊት ጣለ። ከቡድን መሪው አቶ መስፍን አህመድ ጋር ግጭት ውስጥ በመግባት በብዙኃኑ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ ያሬድ ካሳዬ ከክለቡ ማረፊያ ካምፕ እንዲባረር መደረጉ ተሰምቷል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚቀጥሉት ቀናት ከማላዊ አቻው ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ተጫዋቹን በስብስባቸው ውስጥ ሳያካትቱት የቀሩት በትላንትናው ዕለት በፈጸመው ስነምግባር የጎደለው ድርጊት ምክንያት እንደሆነ መረጃዎች ማመላከታቸውን ሃትሪክ ስፖርት ዘግቧል።

#ethiopianfootball #ethiopianpremiereleague #ethiopiainsport #yaredkasaye #ethiopiamedhin #sidamabunafc #hatricksport #walyas #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: