በኢትዮጵያ በቴሌግራም የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊቆም ነው።በቴሌግራም ላይ ክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በኢትዮጵያ በቴሌግራም የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊቆም ነው።
በቴሌግራም ላይ ክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነው ዋሌቴ (Wallet) ከግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) እንደሚያቆም አስታውቋል።
ይህ ውሳኔ የተወሰደው የሀገሪቱን የፋይናንስ ህግ መሰረት አድርጎ እንደሆነ ነው የገለጸው።
ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ሁሉም በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የP2P ማስታወቂያዎች በሙሉ ይጠፋሉ ፤ አዲስ ማስታወቂያዎችንም መለጠፍም አይቻልም ተብሏል።
ከቀነ ገደቡ በፊት የተጀመሩ ግብይቶች በተለመደው አሰራር መሠረት መፈጸም እንደሚቻል ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም ፦
– ቢትጌት
– ባይናንስ
– ኦኬኤክስ
– ባይቢት … የመሳሳሉ መድረኮች በኢትዮጵያን ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶች (P2P) ማቆማቸው ይታወሳል።
አሁን ደግሞ በP2P ግብይት በስፋት የሚታወቀው የቴሌግራም ዋሌት ከግንቦት 25 በኋላ ያቆማል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1