መረጃየኢትዮጵያ መንግሥት እና የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ አበዳሪ ዓለማቀፍ ባለሃብቶች በእዳ አከፋፈል ዙሪያ ሲያደርጉት የቆ…

- Advertisement -
Sidebar AD
መረጃ‼️
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ አበዳሪ ዓለማቀፍ ባለሃብቶች በእዳ አከፋፈል ዙሪያ ሲያደርጉት የቆዩት ሌላ ዙር ድርድር ሳይሳካ ቀረ።
ድርድሩ ያልተሳካው፣ የዓለማቀፍ ቦንድ ያዥዎች መንግሥት በእዳ አከፋፈሉ ዙሪያ አሻሽሎ ያቀረበውን ሀሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።
መንግሥት ሁሉም የውጭ አበዳሪዎች በቡድን 20 የአበዳሪዎች ማዕቀፍ ሥር የእዳ ሽግሽግ ሊያደርጉ ይገባል በሚለው አቋሙ የጸና ሲሆን፣ ኢትዮጵያ አኹንም የአበዳሪዎችን እኩልነት መርህ የሚያረጋግጥ “በገበያ ላይ የተመሠረተ መፍትሄ” ለመተግበር ቁርጠኛ መኾኗን ገልጧል።
ድርድሩ ሲካሄድ የቆየው፣ መንግሥትና የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ባለፈው ጥር ወር በመርህ ደረጃ የደረሱበትን ስምምነት የሁለትዮሽ አበዳሪ አገራት ኮሚቴ ሳይቀበለው ከቀረ በኋላ ነበር።(ዋዜማ)
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1