በኮሪደር የለሙ ቦታዎች ላይ የሲጋራ ቁራጭ መጣል እስከ 2 ሺህ ብር የሚያስቀጣውን መመሪያ ለመተግበር የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
በአዲስአበባ ከተማ በኮሪደር የለሙ ቦታዎች ላይ የሲጋራ ቁራጭን መጣል እስከ 2 ሺህ ብር ቅጣት የሚጥል መመሪያ መውጣቱን ተከትሎ የግንዛቤ እና የቁጥጥር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስአበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።
ከተማዋን የሚመጥን ፅዱ አካባቢ ለመፍጠርና ሁሉም በኮሪደር የሚለሙ ቦታዎች ከሲጋራ ጭስ ነጻ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሆነ የገለፁት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ ናቸው።
በተለይም የደንብ ማስከር ባለስልጣን ጠንከር ያለ የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት ትምባሆን ከአዋኪ ድርጊቶች እንዲካተት በማድረግ እና ከማኅበራዊ ተቋማት እስከ 500 ሜትር ርቀት እንዳይጨስ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑ ትልቅ ለውጥ እንዲመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።
በለሙ የኮሪደር ቦታዎች ላይ የሲጋራ ቁራጭ መጣል እስከ 2ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ ይህንን መመሪያ የማስገንዘብ እና የቁጥጥር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ በአዋጅ 1112/2011 የተቀመጡ ክልከላዎችን ከማስፈፀም አንፃር ጥሩ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንደሚገኝ አክለዋል።
የችግሩን ውስብስብነት በሚመጥን መልኩ ተቋማት ስራውን በቅንጅታዊና በተቋማዊ አሰራር እንዲቀጥሉ ማስቻል እና የቁጥጥር ስራውን በቀን እና በማታ ወጥ በሆነ መልኩ ማካሄድ አሁንም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.