ተቀጥራ ከምሰራበት መኖሪያ ቤት ከ1ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ንብረቶችን የሰረቀች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ተከሳሽ ዓለም ሲሳይ የተባለች የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በልዩ ስሙ አትሌቶች መንደር ነው።

በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ያለ ምንም ተያዥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የአሰሪዎቿን እንቅስቃሴ በሚገባ ስታጠና የቆየችው ተጠርጣሪዋ በተቀጠረች በ9ኛ ቀኗ የተለያዩ አልባሳት እና መዋቢያ ጌጣጌጦችን፣ የአሜሪካን ዶላር 500፣ የቻይና ሀገር ዩዋን 400፣ የህንድ ሩፒ 600 የCCtv ካሜራ ዳይመንድ የጣት ቀለበት በአጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው አንድ ሚሊየን አራት መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ብር (1,423,192.00) የሚያወጡ የተለያዩ ንብረቶችን ሰርቃ ከአካባቢው መሰወሯን የግል ተበዳይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ጎሮ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው አመልክተዋል፡፡

የጎሮ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ ባደረገው ክትትል ተከሳሿን ከነሙሉ ኤግዚቢቱ ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጥቷት የተወሰኑ ኤግዚቢቶችን በመሸሸግ የተባበራትን ተጠርጣሪ ከሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B-95611 አ/አ ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን ጭምር የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ለክፍሉ አቃቤ ህግ በማቅረብ ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡

ህብረተሰቡ ማንኛውንም ዓይነት ቅጥር ሲፈፅም ህጋዊነትን በተከተለ መልኩ ቢሆን የተሻለ መሆኑን ያስገነዘበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላትም ከወንጀል ፈፃሚዎች ጋር በጥቅም ተሳስረው የወንጀል ተጠያቂ ላለመሆን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1