አርቲስት ሰላማዊት ደስታ አረፈች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በፊልም እና በቲያትር ስራዎቿ የምትታወቀው ዝነኛዋ ተዋናይት ሰላማዊት ደስታ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ዛሬ፣ አርብ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት አርፋለች።

የአርቲስቷን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ የአዲስ አበባ ቲያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እና የቅርብ ወዳጆቿ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ይገኛሉ።

የልጅነት ጓደኛዋ ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ እና የሙያ ባልደረቦቿ ደራሲ ውድነህ ክፍሌ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ እንደመሰከሩላት አርቲስት ሰላማዊት ደስታ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪነቷ ጀምሮ በህጻናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት በነበራት ድንቅ የመድረክ ብቃት የምትታወቅ ሲሆን ትሁት፣ ሰው አክባሪና ለሙያዋ ታማኝ የነበረች ጥንካሬዋ የማይረሳ ጥበበኛ ነበረች።

የአርቲስት ሰላማዊት ደስታ የሽኝት ፕሮግራም ነገ፣ ቅዳሜ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ከረፋዱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ውስጥ በቤተሰቦቿ፣ በወዳጅ ዘመዶቿ እና በሙያ አጋሮቿ በተገኙበት ይከናወናል።

በመቀጠልም የቀብር ስነ ስርዓቱ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ታውቋል።

ለአርቲስቷ ቤተሰቦች፣ የስራ ባልደረቦች እና ለመላው አድናቂዎቿ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሷን በሰላም ያሳርፍ።

#አርቲስትሰላማዊትደስታ #የሀዘንመግለጫ #ጥበብ #ሀገርፍቅርቲያትር #ዜናዕረፍት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: