የተክለሃይማኖት የቆብ ልጆች እንዲበተኑ የተክልዬ ወዳጆችማ አይፈቅዱም ፤
ታሪክ የመልክዐ ምድር ውበት ፈዋሽ ጠበል ድንቅ የአብነት ት ቤት ደግሞ የውሃ እጦትና የውሃ ጥም አደጋ
መርሳ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም ከአዲስ አበባ ወደ መርሳ ተጉዘው መርሳ ሲደረሱ ከዋናው መንገድ ወደ አንድ ቅዱስ ተራራ 5ኪሎ ሜትር ሲወጡ በዚያ ውብ በአገር በቀል ዕጽዋት በተሸፈነው ተራራ ላይ 154 ዘመን ያስቆጠረው የጻድቁ አብነ ተክለ ሃይማንት ጽላት ያለበት አንድነት ገዳም ይገኛል ።
በዚህ ገዳም በተጨማሪ የአቡነ ዘርዐ ብሩክ፣ የመጥምቁ ዮሐንስ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽላቶች ይገኛሉ ። በቦታው የሚገኘው ጠበል ከኪንታሮት ከነቀርሳ ከመናፍስተ ርኩስ በሽታ እየፈወሰ አንዳንዱን በምነና እዛው በገዳሙ አገልጋይ አድርጎ አስቀርቶታል ።
የዛሬ 20 ዓመት ገደማ ቦታው ሊጠፋ ታሪኩ ሊረሳ የነበረ ቦታ በሙስሊም ህብረተሰብ ርብርብ ሳይቀር በዝክረ ቅዱሳን በማህበረ ሥላሴ በማህበረ ሐዋርያት እልህ አስጨራሽ የ20 ዓመታት ጉዞ ገዳሙ አሁን ያለበት ሁኔታ ከማስደነቁም በላይ ወደፊት ደብረ ሊባኖስን ይመስላል የሚለው የመናንያኑ ትንቢትና በልማቱ ሲደክሙ የኖሩ አገልጋዮች ተስፋ የደረሰ ይመስላል ።
ታዲያ ይህ የፈውስ ቦታ የአብነት ት/ቤት የተራራ ላይ ከተማ አደጋ ተጋርጦበታል መናንያኑን የሚፈትን የአብነት ተማሪዎቹን የሚበትን ስለዚህም ዛሬም የቦታው ቅድስና ምስጢር የገባቸውና የወደፊቱ ተስፋ የታያቸው በቦታው በረከት የተጠቀሙ አገልጋዮች ማህበራት ከገዳሙ ልማት ኮሚቴ ጋር ሆነው ገዳሙን ከውሃ እጦት ለመታደግ 10 ሚሊየን ለሚጠይቀው የውሃ ፕሮጀክት ግንቦት 29 እና 30/ 2018 ከምሽቱ 1 ስአት ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት(ኦን ላይን) ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጅተው በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን እንድረስላቸው ይሉናል ።
የተክለሃይማኖት የሆነ አለን ይበለን
ገዳሙ እና የገዳሙ የልማት ኮሚቴ
አቢሲኒያ-2555552222
አማራ ባንክ-9900050734076
013200269023200 አዋሽ
1000753661615ንግድ
https://cash.app/$Abunetekleye
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126
Source: GetuTemesgen









No comments yet.