ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሠጠ መግለጫ

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ግንቦት 07/2018 ዓ.ም. “ዴሞክራሲያዊ መብቶች በብሔር ማንነት እና በመንግሥት አሉታዊ ተፅዕኖ ውስጥ መውደቃቸው ምርጫውን ችግር ውስጥ ይከታል” ሲል ባወጣው መግለጫ፤

የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለሐረሪ ክልል ም/ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅ መሆን ለመመረጥ እንደ አስገዳጅ መስፈርት መቀመጥ በኢፌዴሪ ሕገመንግስት የተደነገገውን ዜጎች ያለምንም ዘር፣ ሐይማኖት እና ሌሎች ማንነት ልዩነቶች ሊጎናፀፉት የሚገባን የመምረጥ እና መመረጥ መብትን የሚጥስ መሆኑን ገልፆ መቃወሙ ይታወሳል።

በተጨማሪም በዚሁ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ለሐረሪ ም/ቤት እንደሚወዳደሩ ዕጩዎች የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅነትን እንደ አስገዳጅ መስፈርት ባያስቀምጥም በክልሉ ኢዜማን ወክሎ ለሕ/ተ/ም/ቤት እንዲወዳደር ያቀረብነው እጯችን በሐረሪ ጠ/ፍ/ቤት የወንጀል እና ፍትህ ብሔር ችሎት መዝገብ ቁ 08916 ከሕግ አግባብ ውጪ የሐደሬ ብሔር ተወላጅ አይደሉም በሚል ፓርቲያችን ባልተሣተፈበት እና ባላወቀው ክርክር እጩው እንዳይወዳደሩ ወስኗል።

የውሳኔው ይዘት ምንም እንኳን ስለ ሐረሪ ክልል ም/ቤት ተወዳዳሪዎች የተሰጠ ቢሆንም ለሕ/ተ/ም/ቤት ያቀረብነው አባላችን ስም ተካቶ የተሠጠው ውሳኔ ሕጋዊ ባለመሆኑ ምርጫ ቦርድ ለፍ/ቤቱ ማብራሪያ ቢጠይቅም እንዲሁም ፓርቲያችን በሌለበት የተሠጠው ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑንና የክርክሩ አካል እንድንሆን ያቀረብነውን ጥያቄ ከፍትሕ ይልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተጭኖት ሳይቀበል ቀርቷል።

በመሆኑም ምርጫ ቦርድ የፓርቲያችንን እጩ ተወዳዳሪ ሕጋዊ ባልሆነ/ባልተሠጠ ውሳኔ ላይ በመመሥረት ከእጩነት ማገዱ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ እንዲታረም ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታችንን ያቀረብን ሲሆን ክርክሩ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ የምርጫ ቦርድ እጯችንን ለመሠረዝ የሠጠው ውሳኔ እንዲታገድ የፍ/ቤቱን ውሳኔ የጠየቅን ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግን ተከሳሽ የሆነውን ምርጫ ቦርድን ሳያስቀርብ በእራሡ የተከሳሽን የመከራከርያ ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ አሳልፏል።

የተላለፈው ውሳኔ አግባብነት ያለው እና ፍትሐዊ ነው ብለን የማናምን መሆኑን እየገለጽን ኢዜማ የዚህ ዓይነት ኢፍትሐዊ አሠራሮች ከሀገራችን እስከሚጠፉ ድረስ እስከመጨረሻው ድረስ እንደሚሞግት ለመግለጽ ይወዳል።

#ኢዜማ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: