የምንጠቀማቸው ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርሞች የየትኞቹ ሀገራት ስሪት ናቸው?
በዕለት ተዕለት ሕይወታችን መረጃ ለመለዋወጥ፣ ለስራ እንዲሁም ለመዝናኛ የምንጠቀማቸው ግዙፍ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ከጀርባቸው የሀገራት የቴክኖሎጂ ልዕልና ፍልሚያ ያለባቸው መሆኑ ይታወቃል።
ለመሆኑ እነዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪ የዲጂታል መድረኮች የማን ሃገር ስሪት ናቸው?
በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያሏቸው እንደ ፌስቡክ (Facebook)፣ ዩቲዩብ (YouTube)፣ ኤክስ (X – የቀድሞው ትዊተር) እና ሊንክድኢን (LinkedIn) ያሉ መድረኮች ሙሉ በሙሉ የቴክኖሎጂዋ መዲና የአሜሪካ ስሪቶች ናቸው።
እነዚህ መድረኮች በሜታ፣ ጎግል እና ማይክሮሶፍት በመሳሰሉ የአሜሪካ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ባለቤትነት ስር የሚተዳደሩ ሲሆን፣ ዋና መሥሪያ ቤቶቻቸውም በካሊፎርኒያ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል በአጭር ቪዲዮዎቹ ዓለምን እያናወጠ የሚገኘው ታዋቂው ቲክቶክ (TikTok) የቻይና ስሪት ነው።
መተግበሪያው ባይትዳንስ (ByteDance) የተሰኘው የቻይና ኩባንያ ንብረት ቢሆንም፣ ከአሜሪካና አውሮፓ የደህንነት ስጋት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ስራዎቹን ከሎስ አንጀለስ እና ከሲንጋፖር ሆኖ ያከናውናል።
ለብዙዎቻችን የቅርብ ረዳት የሆነው ቴሌግራም (Telegram) ደግሞ አመጣጡ የሩሲያ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ይፋዊ የዱባይ (የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ) ስሪት ተደርጎ ይወሰዳል።
@Seledadotio

No comments yet.