ምርጫ ቦርድ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ “መንገድ ተዘግቶብናል” ስለመባሉ የደረሰኝ ይፋዊ ሪፖርት የለም አለ
በመጪው ሰኞ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሎጂስቲክስ ስርጭት እየተከናወነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት “መንገድ ተዘግቶብናል” ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ እስካሁን የደረሰ ይፋዊ ሪፖርት አለመኖሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የሎጂስቲክስ ስርጭቱ በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን ትናንት ምሽት በሰጡት ማብራሪያ ቢገልጹም፣ በአማራ እና በጋምቤላ ክልሎች በሚገኙ ዘጠኝ የምርጫ ክልሎች ላይ ግን እስካሁን የምርጫ ቁሳቁስ አለመድረሱን አምነዋል።
በተለይም በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ያስተላለፈውን የእንቅስቃሴ ገደብ ተከትሎ “መንገዶች ተዘግተውብናል” እየተባለ ስለሚነሳው ቅሬታ ከተጠየቁ በኋላ፣ ሰብሳቢዋ በሰጡት ምላሽ በእንቅስቃሴ ገደቡ ምክንያት የደረሰባቸውን መስተጓጎል በተመለከተ እስካሁን ድረስ ወደ ቦርዱ የመጣ ይፋዊ ሪፖርት የለም ብለዋል።
ይሁን እንጂ ሰብሳቢዋ አክለው እንዳረጋገጡት፣ በአማራ ክልል ከሚገኙ 48 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በጸጥታ ምክንያት ምዝገባ ዘግይቶ በነበረባቸው 40 ክልሎች ላይ ብቻ ምዝገባ መከናወን የቻለ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 8 የአማራ ክልል የምርጫ ክልሎች ግን ዘንድሮ ምርጫ የማይካሄድባቸው መሆኑ ታውቋል።
በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እና በአማራ ክልል በተወሰኑ 8 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ባለመካሄዱ ምክንያት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች ውስጥ በ501 ወንበሮች ላይ ብቻ ውድድር ይካሄዳል። የትግራይ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አባል ያልነበረው ሲሆን፣ በዘንድሮውም ምርጫ ምንም ዓይነት ተወካይ የማይኖረው መሆኑ ተረጋግጧል።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ቦርዱ አስታውቋል። ቦርዱ ቀደም ሲል የገለጸው የመራጮች ቁጥር 50.5 ሚሊዮን የነበረ ቢሆንም፣ በልዩ ሁኔታ የተመዘገቡትን ጨምሮ አሁን ላይ የመጨረሻው የተሟላ ቁጥር ይፋ ሆኗል።
በልዩ ሁኔታ ከተመዘገቡት ውስጥ ከ120 ሺህ በላይ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ያሉ ሲሆኑ፣ ከ20 ሺህ በላይ ደግሞ ተማሪዎች ናቸው። ምርጫውን ለማስፈጸም ከ369 ሺህ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና ከ52 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል።
የምርጫውን ሂደት በታማኝነት ለመታዘብ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ቦርዱ ገልጿል።
55 የአገር ውስጥ የሲቪክ ማኅበራት ሥራቸውን የጀመሩ ሲሆን፣ 1,572 አስተባባሪዎችን እና 64,770 ቋሚና ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎችን በየምርጫ ጣቢያዎቹ ያሰማራሉ።
በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራውና 59 አባላት ያሉት የአፍሪካ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን፣ እንዲሁም በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ዋንዲራ ስፔሲዮዛ(ዶ/ር) የሚመራው ባለ 26 አባላት የኢጋድ ዓለም አቀፍ ታዛቢ ቡድን በይፋ ሥራ ጀምረዋል።
ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎችና ታዛቢዎች ሂደቱን እንዲታዘቡ ለማስቻል ከ250 ሺህ በላይ የመለያ ባጆችን እያሰራጨ ሲሆን፣ ይህ ስርጭት በፓርቲዎች ጥያቄ መሠረት በሚቀጥሉት ሁለት ቀናትም እንደሚቀጥል ታውቋል።
በዘንድሮው ምርጫ ላይ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ጥምረቶች ይገኛሉ። (አንደኛው ጥምረት 8 ፓርቲዎችን፣ ሁለተኛው ጥምረት ደግሞ 4 ፓርቲዎችን በአንድነት ያቀፉ ናቸው)። ለምርጫው በአጠቃላይ 10,438 የፓርቲ ዕጩዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ በተጨማሪ 80 የግል ዕጩዎች በምርጫው እንደሚሳተፉ በትናንቱ መግለጫ ተመላክቷል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.