ቡዳፔስት :አርሰናል እና ፒኤስጂ ለታሪካዊው ድል ይጋጠማሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የ2025/26 የውድድር ዘመን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊን የሚለየው ተጠባቂ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና በአርሰናል መካከል በሀንጋሪ ቡዳፔስት ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም ይካሄዳል።

ጨዋታውን ጀርመናዊው የ42 ዓመት ዳኛ ዳንኤል ሴበርት በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የአምናው የውድድር ዓመት ሻምፒዮን ፒኤስጂ ዋንጫውን በእጁ ለማቆየት ወደ ሜዳ ይገባል።

የፈረንሳዩ ክለብ በግማሽ ፍጻሜው የጀርመኑን ባየርን ሙኒክ በድምር ውጤት በመርታት ለዚህ ማጠቃለያ ጨዋታ የበቃ ሲሆን በዘመኑ የውድድር ሂደት 44 ግቦችን በማስቆጠር በአጥቂ መስመር ብቃቱ ቀዳሚ ሆኗል።

ቡድኑ 22 ግቦች የተቆጠሩበት ቢሆንም የባሎንዶር አሸናፊው ኦስማን ዴምቤሌ፣ ኪቪቻ ክቫረትስኬሊያ፣ ኔቬስ፣ ቪቲኒሃ እና ዴዝሪ ዱዌ ያሉበት አስፈሪ የማጥቃት ኃይል አለው።

ከጉዳት የተመለሱት ኦስማን ዴምቤሌ እና አሽራፍ ሀኪሚ ለአሰልጣኙ ተጨማሪ ጥንካሬ ሆነዋል።

በሌላ በኩል የእንግሊዙ አርሰናል በግማሽ ፍጻሜው የስፔኑን አትሌቲኮ ማድሪድ በማሸነፍ ከ20 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደርሷል።

በቅርቡ ከ22 ዓመታት ቆይታ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በማንሳት 14ኛ የሀገር ውስጥ ስኬቱን ያመዘገበው መድፈኞቹ አሁን ደግሞ የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ታላቅ ዋንጫ (Double) ለመደገም አልመዋል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል በዚህ የውድድር ዘመን በሻምፒዮንስ ሊጉ እስካሁን አንድም ጨዋታ አልተሸነፈም።

በውድድሩ 29 ግቦችን አስቆጥሮ 6 ግቦች ብቻ የተቆጠሩበት ጠንካራ የተከላካይ ክፍል ያለው ሲሆን የግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ድንቅ ብቃት እንዲሁም የጋብሬል ማጋሌሽ እና የዊሊያም ሳሊባ የኋሊት መስመር ጥምረት በዛሬው ጨዋታ የፒኤስጂን ፈጣን ጥቃት ለመግታት ትልቅ ሚና ይጫወታል።

አርሰናል ከአውሮፓ መድረክ ጋር ያለው የታሪክ ቁርኝት የደበዘዘ በመሆኑና ከዚህ ቀደም ያሸነፋቸው የ1970/71 የኢንተር ሲቲስ ፌርስ ካፕ እና የ1993/94 የካፕ ዊነርስ ካፕ ዋንጫዎች በአሁኑ ወቅት የማይሰሩ በመሆናቸው ይህ ጨዋታ ለክለቡ አዲስ ታሪክ የመጻፊያ ትልቅ ዕድል ነው።

ሁለቱ ክለቦች ባደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስ በርስ ግንኙነቶች በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ጊዜ ሲሸናነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በሚጀመረው ጨዋታ አርሰናል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ንጉስ ለመሆን ፒኤስጂ ደግሞ ለተከታታይ ዓመት ታሪኩን ለማደስ ብርቱ ፍልሚያ ያደርጋሉ።

#አርሰናል #ቻምፒዮንስሊግ #ሚኬልአርቴታ #ቡዳፔስት2026 #የእግርኳስዜና #አውሮፓሻምፒዮንስሊግ #ፒኤስጂ #የስፖርትዜና #Arsenal #PSG #UCL
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: