ዓለም ሙሉ በጉጉት የሚጠብቀው ጨዋታፒኤስጂ ወይስ አርሰናል – ማን ሻምፒዮን ይሆናልየ2025/26 የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒ…

- Advertisement -
Sidebar AD

ዓለም ሙሉ በጉጉት የሚጠብቀው ጨዋታ
ፒኤስጂ ወይስ አርሰናል – ማን ሻምፒዮን ይሆናል
የ2025/26 የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በፒኤስጂ እና አርሰናል መካከል ይደረጋል፡፡
የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ ለተከታታይ የውድድር ዓመት ሻምፒዮን ለመሆን ይፋለማል፡፡
የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ በግማሽ ፍጻሜው የጀርመኑን ክለብ ባየርን ሙኒክ በድምር ውጤት በማሸነፍ ለፍጻሜ መብቃቱ ይታወሳል፡፡
ፒኤስጂ በውድድር ዓመቱ እስካሁን ድረስ 44 ግቦችን ተጋጣሚዎቹ ላይ ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡
በርካታ ግቦችን ተጋጣሚዎቹ ላይ ያስቆጠረው ፒኤስጂ 22 ግቦች ደግሞ ተቆጥረውበታል፡፡
የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል በግማሽ ፍጻሜው የስፔኑን ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ በድምር ውጤት በመርታት ለፍጻሜ መድረሱ አይዘነጋም፡፡
ከ20 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ የደረሰው አርሰናል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረኩ ሻምፒዮን ለመሆን ይፋለማል፡፡
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል በዚህ የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መድረክ እስካሁን ድረስ አንድም ጨዋታ አልተሸነፈም፡፡
አርሰናል 29 ግቦችን ተጋጣሚዎቹ ላይ ሲያስቆጥር 6 ግቦች ብቻ ተቆጥረውበታል፡፡
በጨዋታው የስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ድንቅ ብቃት፣ የጋብሬል ማጋሌሽ እና የዊሊያም ሳሊባ አስደናቂ ጥምረት ይጠበቃል፡፡
ጠንካራው የአርሰናል የተከላካይ ክፍል አስፈሪ የፊት መስመር ጥምረት ያለውን የፒኤስጂ የማጥቃት እንቅስቃሴ ለማስቆም በጨዋታው ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቀዋል፡፡
ጨዋታው በሀንጋሪ ቡዳፔስት ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ ይደረጋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1