የእንግሊዝ መንግሥት የስደተኞችን ዕድሜ ለመለየት የኤአይ ቴክኖሎጂ ሊጠቀም ነው።የእንግሊዝ መንግሥት በድንበር ላይ ያሉ ጥገኝነት…

- Advertisement -
Sidebar AD
የእንግሊዝ መንግሥት የስደተኞችን ዕድሜ ለመለየት የኤአይ ቴክኖሎጂ ሊጠቀም ነው።
የእንግሊዝ መንግሥት በድንበር ላይ ያሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ዕድሜ በኤአይ (AI) ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ አስጀምራለሁ ብሏል።
ቴክኖሎጂው በድንበር ላይ የተነሱ ፎቶግራፎችን በመተንተን የሰውን ዕድሜ የሚመረምር ሲሆን ከዚህ ቀደም ለዚሁ አገልግሎት ሥራ ላይ ከዋሉ የሰነድ ምርመራ እና የህክምና ምርመራዎች (ኤክስ-ሬይ እና ኤም.አር.አይ) የሚያግዝ ተጨማሪ አማራጭ ነው ተብሏል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ እስከ መጋቢት 2026 ባለው መረጃ መሠረት  ከ6,400 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ እንግሊዝ ህጻን ነን ብለው በማቅረባቸው ዕድሜያቸው ተጣርቷል። ከእነዚህ ውስጥ 43 በመቶ የሚሆኑት አዋቂዎች መሆናቸው ተረጋግጧል።
የቴክኖሎጂው ዝግጅት እና የሶስት ዓመት የሙከራ ጊዜ በድምሩ 322,000 ፓውንድ ወጪ እንደሚጠይቅ ሲሆን የሙከራ ሂደቱ በሚቀጥለው ዓመት ይጀምራል ተብሏል።
የአገሪቱ የድንበር ደኅንነት እና ጥገኝነት ሚኒስትር አሌክስ ኖሪስ፣ አዋቂዎች የሐሰት ዕድሜ በመጥቀስ ሥርዓቱን መበዝበዛቸው ለህጻናት መድረስ የነበረበትን ድጋፍ እያስተጓጎለ መሆኑን በመጥቀስ፣ ቴክኖሎጂውን መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።
Source : BBC
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: