ጋና አፍሪካውያን ለስራም ሆነ ለሽርሽር ብቅ ቢሉ የማስከፍላቸው ነገር ትቼዋለሁ አለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና፤ የቪዛ ማጽደቅ ሂደትን ለማፋጠን፣ ጉዞን ለማቅለልና የኢሚግሬሽን አሠራርን ለማዘመን የሚያስችል አዲስ የኤሌክትሮኒክ ቪዛ (e-visa) መድረክን በይፋ አውጅዋለች።

ይህ እርምጃ የተወሰደው የአፍሪካ መንግሥታት ቱሪስቶችን፣ ባለሀብቶችን፣ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን እና የአህጉሪቱን ተጓዦች ለመሳብ በሚወዳደሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ የኢ-ቪዛ ጋናን ለአህጉራዊ ንግድ እና ቱሪስት መግቢያ በር ለማድረግ እየተደረገ ያለው ሰፊ ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።

እርምጃው ባለፉት ዓመታት በአፍሪካ ኅብረት ውህደት ጥረቶች ቢደረጉም አሁንም በዓለም ላይ ከፍተኛ ገደብ ያለበትን የአፍሪካ የእርስ በርስ ጉዞ፣ የወረቀት ሥራዎችን፣ ረጅም የኤምባሲ ሂደቶችንና የጉዞ ጋሬጣዎችን በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል።

ፕሬዚዳንት ማሃማ አክለውም ለቱሪዝምም ሆነ ለንግድ ሥራ ወደ ጋና ለሚጓዙ የአፍሪካ ፓስፖርት ባለቤቶች የቪዛ ክፍያ መነሳቱን ያበሰሩ ሲሆን፤ ይህም ውሳኔ ጋናን የቀጣናው የንግድና የጉዞ ማዕከል የማድረግ ዕድሏን እንደሚያጠናክረው ተገልጿል።

ይህ ማሻሻያ የመጣው የአፍሪካ አገራት የድንበር አስተዳደርን ለማሻሻል፣ የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ እና ለውጭ ኢንቨስትመንት ለመወዳደር የዲጂታል ኢሚግሬሽን ሥርዓቶችን እየተጠቀሙ ባሉበት ወቅት ነው።

እንደ ኮትዲቯር፣ ኬንያ እና ሩዋንዳ ያሉ አገራት መንግሥታት በቅርቡ በAfCFTA ሥር አህጉራዊ ንግድና እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ የዲጂታል ቪዛ ፖሊሲዎቻቸውን ማስፋፋታቸው ወይም የጉዞ ገደቦችን ማላላታቸው ይታወሳል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#ቅዳሜገበያ#etbusinessview
#Ethiopia#Africa #Ghana


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: