#Ethiopia | በፓሪስ ሳን ዠርሜን እና በአርሰናል መካከል የሚደረገው አጓጊ የባለቤትነት ፍልሚያ መደበኛው 90 ደቂቃ እንዲሁም የተሰጠው ባለ ስድስት ደቂቃ ተጨማሪ ሰዓት ያለ አሸናፊ በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ 30 ደቂቃ ተጨማሪ ሰዓት አምርቷል።
በጨዋታው ሂደት የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ፍጹም የበላይነትን ያሳየ ሲሆን 72 በመቶ የኳስ ቁጥጥር ድርሻ ነበረው። ቡድኑ ካደረጋቸው 16 የግብ ሙከራዎች መካከል ሦስቱ ኢላማቸውን የጠበቁ ነበሩ። በተጨማሪም 93 በመቶ ስኬታማነት የነበረው 618 ቅብብሎችን ከማድረጉም በላይ 10 የማዕዘን ምቶችን አግኝቷል።
በአንጻሩ የእንግሊዙ አርሰናል በ28 በመቶ የኳስ ቁጥጥር የተወሰነ ሲሆን መላው ጨዋታውን ያጠናቀቀው በሦስት የግብ ሙከራዎች ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ካደረጋቸው ሙከራዎች መካከል አንዷ ኢላማዋን ጠብቃ ወደ ግብነት ተቀይራለች። ቡድኑ በጨዋታው ምንም ዓይነት የማዕዘን ምት አላገኘም።
በአኃዛዊ መረጃዎች ላይ ሰፊ የብልጫ ልዩነት ቢታይም መደበኛው ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ሁለቱም ክለቦች ቀሪዎቹን 30 ደቂቃዎች ተጠቅመው ድል ለመቀዳጀት ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ።
የጨዋታው ሌላኛው ገጽታ በነበረው የጥፋት ምዝገባ ፒኤስጂ ዘጠኝ እንዲሁም አርሰናል 11 ጥፋቶችን የፈጸሙ ሲሆን በዚህም ምክንያት ለአርሰናል ተጫዋቾች ሁለት ቢጫ ካርዶች፣ ለፒኤስጂ ደግሞ አንድ ቢጫ ካርድ ተመዝግቧል።
#UCL #PSG #Arsenal #Football #Soccer #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.