ካናዳዊዉ ራፐር ድሬክ አርሰናል ፒኤስጂን ያሸንፋል ብሎ 1.5 ሚሊዮን ዶላር አስይዟል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከአለማችን እዉቅ ራፐሮች አንዱ የሆነዉ ካናዳዊዉ ድምጻዊ ድሬክ አርሰናል የምሽቱን የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂን ረትቶ ሻምፒዮን ይሆናል ሲል 1.5 ሚሊዮን ዶላር ማስያዙ ተዘግቧል።

ድሬክ 1 ሚሊዮን ዶላሩን በቀጥታ አርሰናል የምሽቱን ፍጻሜ ያሸንፋል ፣ እንዲሁም ቡካዮ ሳካ አሲስት ወይም ግብ ያስቆጥራል ብሎ ያስያዘዉ ሲሆን ቀሪዉን 500 ሺህ ዶላር ደግሞ አርሰናል ጨዋታዉን 1 ለ 0 ያሸንፋል ሲል መድቦበታል።

ድሬክ ከዚህ ቀደም በስፖርታዊ ዉርርዶቹ ቀንቶት አያዉቅም ይባላል። እርሱ በተደጋጋሚ ያሸንፋሉ ብሎ ገንዘቡን ያስያዘባቸዉ ክለቦች ድል ሲቀናቸዉ አልታየም።

በ 2022 አርሰናል ሊድስን ያሸንፋል ብሎ አስይዞ ድል ቀንቶት የነበረ ቢሆንም በተመሳሳይ ትኬት ግን ባርሴሎና ሪያልማድሪድን ያሸንፋል ብሎ አስይዞ ባርሳ ተረትቶ ነበር። በተለያዩ የቦክስ ጨዋታዎችም ድሬክ በመቶሺዎች ያስያዘበት ተጨዋች በተደጋጋሚ ሲረታ እንጂ ሲያሸንፍ አልታየም።

ብዙሃኑ የስፖርት አፍቃሪያኖችም “የድሬክ እርግማን” ሲሉ ሽንፈቱን ይጠሩታል። ድሬክ ገንዘብ ያስያዘበት ቡድን ይረታል እንደማለት ነዉ።

ድሬክ ድል ይቀናው ይሆን?

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#Selamshowbiz


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1