የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ከአንገቱ የወጣው ደም እሳት ሆኖ አጥፍቷቸዋል

በ277 ዓ.ም ጥር 20 ፍልስጤም ልዩ ስሟ “ልዳ” የተወለደው ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ካላቸው ሰማዕታት ቀዳሚው ነው፡፡ የአባቱን ሞት ተከትሎ ከሌላ መኳንንት ጋር ያደገው ጊዮርጊስ የክርስትና ጠላት ከሆነው ዱዲያኖስና ከ70ው ነገስታት ጋር የተጋፈጠው የአባቱን ምስፍና እንዲሰጡት ሊጠይቅ በሔደበት ክርስቲያኖችና ክርስትና ሲገፉ በማየቱ ነው፡፡ ጊዮርጊስ ማለት “ብሩህ ኮከብ፣ ፀሐይ” ሲሆን ተጋድሎውን ሲጀምር የሃያ ዓመት ወጣት ነበር፡፡ በቤሩትም የሚመለክና ሴት ልጆቻቸውን የሚገብሩለትን ደራጎን ገድሎ ሕዝቡን ወደ ክርስትና አስገባቸው፡፡ በነገሥታቱ ፊትም የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡

ምንም እንኳን ንጉሡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመሣፍንት ወገን መሆኑን እንደ መግቢያ በመጠቀም ሊያባብለው ቢሞክርም “አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም” ብሎ በእምነቱ ጸና፡፡ ዱድያኖስም ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን ያደርስበት ጀመር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ያጸናው ቍስሉንም ያድነው ነበር፡፡ ሦስት ጊዜ እንደሚሞት እርሱም እንደሚያስነሣው በአራተኛውም የሰማዕትነትን አክሊል እንደሚቀበል ነገረው፡፡ ቃል ኪዳንም ገባለት፤ ለሰባት ዓመትም በጽኑዕ መከራና በሥቃይም እንዲሁም በተጋድሎ እንደሚኖር በዚያም ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ እንደሚሆን መላእክትም እንደሚያገለግሉትም ነገረው፡፡ ንጉሥ ዱድያኖስም ቅዱስ ጊዮርጊስ ትእዛዙን ባለመቀበሉ ተቆጥቶ አትናስዮስ የሚባል ታላቅ መሠሪ አስጠርቶ በፍጥነት የሚገድል መርዝ ቀምሞ በጽዋ መልቶ አጠጣው፡፡

መርዙ ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ቀረ፡፡ ያ መሠርይም ይህን ድንቅ ሥራ ሲያይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ የሚሆኑ ሌሎች ሰዎች ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ሞተው የሕይወትን አክሊል ተቀዳጁ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ለሰባት ዓመታት በቅድስና ሲጋደል ቆይቶ፣ ታላቅ የምህረት ቃል ኪዳን ተቀብሎ ሚያዝያ 23 ቀን በሰይፍ አንገቱን ተመቶ ሲሞት ከአንገቱ የወጣው ደም እሳት ሆኖ ሰባውን ነገስታት አጥፍቷቸዋል፡፡ ስለክርሳቶስ ፍቅር ዓለምን የናቁ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው የዓለም ደስታቸውን ስለክርስቶስ ፍቅር ትተዋልና በረከታቸው ብዙ ነው፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1