#Ethiopia | ስታዲየሙ ከ 67,000 በላይ ተመልካች የመያዝ አቅም ቢኖረውም ለደጋፊዎች የተሰጠው 39,000 መቀመጫ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
ፒኤስጂ እና አርሰናል ለእያንዳንዳቸው 17,200 የመግቢያ ትኬት እንደተሰጣቸው ተነግሯል።
በተጨማሪም 5,000 ትኬቶች በዓለም ላይ ላሉ እግርኳስ ደጋፊዎች መከፋፈሉ ነው የተገለጸው።
ሁሉም ቀሪ የመግቢያ ትኬቶች የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር እና ለአጋሮቹ መሆናቸው ተነግሯል።
የፍፃሜ ተፋላሚ ክለቦች አነስተኛ ትኬት ማግኘታቸው ዩኤፋን በየአመቱ የሚያስተቸው ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል።
የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ለደጋፊዎች ጥቂት ትኬት ብቻ መስጠቱን በርካቶች ተቃውመውታል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#tikvahethsport
Source: GetuTemesgen









No comments yet.