ለወጣቶች እና የሚዲያ ተቋማት በስደት አስተዳደር ዙሪያ የሚዲያ ንቅናቄን ለማጠናከር የስትራቴጂክ አጋርነት ውይይት ተካሄደ።

- Advertisement -
Sidebar AD

ውይይቱ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ አተኩረው በሚሰሩት ሲግማ ኢስት አፍሪካ እና ስዊት ላይፍ ፎር ኦል Sweet Life for All Charity Organization የተሰናዳ መሆኑ ተጠቁሟል ።

ተቋማቱ “ይመለከተኛል” ሲሉ ከዚህ ቀደም አብረው መስራታቸውን በመጥቀስ በመድረኩ እኤአ 2025–2026 ዓ.ም የ“Digital Voices, Real Impact” ዘመቻ የተገኙ ውጤቶች፣ የስደት ጉዳይ ላይ የሚዲያ ሚና፣ የወጣቶች አቅም ግንባታ፣ የሰው ዝውውር እና የህገ-ወጥ ስደት መከላከል እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ያለው የተቀናጀ ክልላዊ ምላሽ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ተወክለው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ደረጀ ተግይበሉ “እንደዚህ ያሉ መድረኮችን ለማገዝ መረጃዎችን በማቅረብ ፣ ግንዛቤን ከመፍጠር አንፃር እንዲህ ያለው ምክክር እና ስትራቴጂክ አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።”

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዬሀንስ ብርሀኑ መከላከል ፣ከለላ እና ጥበቃ ቅንጅታዊ አሰራር ፣ የህግ ተጠያቂነት፣ በጋራ መስራት ላይ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በዘርፉ የረጅም አመት የስራ ልምድ ያላቸው የውዲንዳድ ሀላፊ እና የምስራቅ አፍሪካ ስትራቴጂክ ተወካይ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ሽፈራው ሀገራዊ ምላሹ እንዳለ ሆኖ ቀጠናዊ ጉዳይ ላይም አብሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል ።

የ Sweet Life for All Charity Organization መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አንተነህ ተስፋዬ በንግግራቸው፣ “ዲጂታል ሚዲያ የማህበረሰብ ንቅናቄ መፍጠሪያ እና የወጣቶች ድምፅ ማጉሊያ ኃይለኛ መሳሪያ ነው በማለት በተለይ በፍልሰት እና በህገወጥ ሰው ዝውውር ጉዳዮች ላይ የተቀናጀ የሚዲያ ተሳትፎ ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ SIGMA EAST AFRICA CHARITABLE ORGANIZATION FOUNDER AND
CEO የሲግማ ኢስት አፍሪካ መስራች እና ስራ አስኪያጅ በፍልሰት ዙሪያ ሀገራዊና ቀጠናዊ ምላሾች ላይ አብሮ መስራቱ በከፍተኛ ትኩረት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማመላከቱ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል ።

በውይይቱ ውስጥ የስደት አስተዳደር፣ የተመላሽ ዜጎች ድጋፍ፣ የወጣቶች ስራ ፈጠራ፣ የሚዲያ ተሳትፎ እና የህገወጥ የሰው ዝውውር ግንዛቤ ማስፋፊያ ላይ በባለሙያዎች የተመራ ውይይት ተካሂዷል።

ሲግማ ኢስት አፍሪካ እና ስዊት ላይፍ ፎር ኦል የተሰኙት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የምስረታ እድሜያቸው አጭር ቢሆኑም በእቅድ እና በተግባራዊ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸውም ተገልጿል ።

በዛሬው ውይይት ሀገራችን ኢትዮጵያ በሰዎች ዝውውር እያደረገችው ስላለ እንቅስቃሴ እና ስለመጣ ለውጥ የተነሳ ሲሆን ተቋማቱ ከአጋር አካላት ጋር የሰሩትን በቀጣይም በተለያዩ ሀገራት በተለይም በአረቡ አለም በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቻችን ድምፅ ለመሆን ንቅናቄም ለመጀመር ከስምምነት ተደርሷል።

ዝግጅቱ በአዲስ አበባ ማግኖሊያ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ከመንግስት ተቋማት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ፣
ሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናስ ቢሮ ፣ ከሚዲያ ተቋማት፣ ከሲቪል ማህበራት፣ ከወጣቶች አደረጃጀት እና ከአለም አቀፍ አጋሮች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ አምስት ተቋማት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል ።
በስተመጨረሻም ሁለቱ ተቋማት ላስመዘገቡት ውጤት በሥራ እንቅስቃሴያቸው ደጋፊ ለነበሩ ተቋማትና ግለሰቦች የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክተዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: