በደቡብ አፍሪካ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን የደህንነት ዋስትና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ስደተኞች እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተሰጠውን የማስጠንቀቂያ ገደብና በዜጎች ላይ እያነጣጠረ የመጣውን ማዋከብ ለመግታት በሀገሪቱ ከሚገኙ ተቋማት ጋር ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

ወደ ደቡብ አፍሪካ የሄደው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን የዜጎችን ደህንነት ጥበቃ በሚመለከት ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ግንኙነትና ትብብር ዲፓርትመንት፣ የድንበር አስተዳደር ባለሥልጣን፣ የደቡብ አፍሪካ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ተወካዮች ጋር ነው ውይይቱን ያደረገው፡፡

ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት ስደተኞችን ባነጣጠረ መልኩ የማዋከቡ ተግባር፣ የዜጎችን ኃብት እና ንብረት እስከ መዝረፍ እንዲሁም ሥራ እስከ መከልከል ደረጃ መደረሱ የሚታወስ ሲሆን ፥ ሰነድ የሌላቸው ዜጎችም በሀገሪቱ ሕግና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት እንዲስተናገዱና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ከስምምነት መድረሳቸውን ጣቢያችን ለማወቅ ችሏል።

ማንኛውም ሕገ-ወጥነት በሕገ-ወጥ መንገድ ሊፈታ እንደማይገባ የገለጹት ሁለቱ ወገኖች፤ በተለይም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሌሎች ወንጀሎች ላይ በተሰማሩ አካላት ላይ የተቀናጀና የማያዳግም የሕግ እርምጃ ለመውሰድም ተስማምተናል ነው ያሉት ሲል አራዳ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2