የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት ሳይጠናቀቅ ለማካሄድ ማቀዱን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ይኽንን የገለጹት የሃይማኖት ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበራት አጀንዳዎች በቀረቡበት የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው።
የምክክር ሂደቱን የሚያሳልጡ 192 አመካካሪ ባለሙያዎች ተመርጠው ሥልጠና መውሰዳቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። በቀጣይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰላምና ምክክር ላይ በሚሠሩ ተቋማት ተጨማሪ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ በአጠቃላይ አራት ሺሕ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምክክር ሂደቱም አምስት መቶ ተሳታፊዎችን በያዙ ስምንት ንዑሳን ጉባኤዎች ተከፋፍሎ የሚካሄድ ሲሆን የውይይቶቹ ማጠቃለያ ምክረ ሐሳብም ይቀርባል።
ኮሚሽኑ የጉባኤውን ዝርዝር መረጃ የዝግጅት ሥራውን እንዳጠናቀቀ ይፋ እንደሚያደርግ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጨምረው ገልጸዋል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.