#Ethiopia | የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አስር ወራት ውስጥ ፍትሐዊ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓትን በመከተል ካቀደው ዕቅድ በላይ 105 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጿል።
የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ መሰረት መንግስቱ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ውስጥ 5 ነጥብ 45 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የተከናወነው ተግባር ግን 5 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ አስችሏል።
ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 43 ቢሊየን ብር ወይም የ74 በመቶ የገቢ ዕድገት ያሳየ መሆኑን ምክትል ሥራ አስኪያጇ አስረድተዋል።
ለዚህ ስኬታማ ውጤት መገኘት ዋናው ምክንያት የጽሕፈት ቤቱ አመራሮች ለዕቅዱ መሳካት ያሳዩት ቁርጠኝነት መሆኑንና ሠራተኞችን በአንድ ዓላማ ሥር በማስተባበር ሌት ተቀን በቅንጅት እንዲሠሩ ማስቻላቸው እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ዕለታዊ የሥራ እንቅስቃሴዎችን በቅርብ መከታተል፣ አፈጻጸሞችን መገምገምና የሚታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ ማረም የሚያስችል የተደራጀ የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት መዘርጋቱ ለውጤታማነቱ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የታክስ ሕግን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለማስከበር ትኩረት ሰጥቶ የሠራ ሲሆን ለግብር ከፋዮች ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት በተደረገው ጥረትም አበረታች ለውጦች መመዝገባቸው ተመልክቷል።
#የአዲስአበባገቢዎች #የካክፍለከተማ #ገቢአሰባሰብ #ታክስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.