ፒኤስጂ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በፓሪስ ሁከት ተቀሰቀሰ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የፓሪሰን ዠርሜን (PSG) የሻምፒዮናነት ድልን ተከትሎ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ እና በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ስርዓት አልበኝነት እስካሁን 416 ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

​ከታሰሩት ደጋፊዎች መካከል 283ቱ በፓሪስ ከተማ ውስጥ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ድርጊቱን ለማስቆም በነበረው ግጭት ሰባት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

​የክለቡ ደጋፊዎች በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው አራት ዋና ዋና የቀለበት መንገዶችን ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን፥ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ የነበረው የእልልታና የደስታ አገላለጽ እስከ ንጋት ድረስ ቀጥሎ አድሯል።

​በሌላ በኩል ፒኤስጂ ይፋዊ የዋንጫ ድሉን በፓሪስ በሚገኘው “Champ-de-Mars” ክፍት የሕዝብ መናፈሻ በጎዳና ላይ እንደሚያከብር ታውቋል።

​በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ የድል ክብረ በዓል ላይ እስከ 90,000 የሚደርሱ የክለቡ አድናቂዎችና ነዋሪዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#PSG #Paris #Ligue1 #FootballNews #France #BreakingNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: