ታዛቢዎቼ ተደብድበዋል-ጎጎት#የምርጫ ታዛቢዎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ጎጎት ፓርቲ ከሰሰ!!!በማእከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ምርጫ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ታዛቢዎቼ ተደብድበዋል-ጎጎት‼️
#የምርጫ ታዛቢዎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ጎጎት ፓርቲ ከሰሰ!!!
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ሲል ጎጎት ፓረቲ ገለጸ። ፓረቲው በኦፊሸል የፌስ ቡክ ገጹ እንዳብራራው “ፓርቲዉ ይንቀሳቀስበት የነበረዉ ሞተር ተነጥቋል።
የምርጫ ወረቀት በፌስታል ይዘዉ ሲበትኑ ተመልክተናል። ለምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲቆም አሳዉቀናል” ብሎ፣ከምርጫ ቦርድ አፍጣኝ ምላሽ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
በስፍራው የምትገኘው የሪፖርተር ዘጋቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ምርጫ አስተባባሪ አቶ ነጋሽን አነጋግራቸው በሰጡት ምላሽ፣ ጎጎት ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ከተማ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ማለቱን ተከትሎ ወደ ቦታው አስተባባሪዎች ልከው እንዳጣሩና ምንም ነገር እንዳልተደረገ ማረጋገጣቸውንተናግረዋል፡፡
ፓርቲው ይህ ሆኗል ባለበት የምርጫ ጣቢያ ሁለት ታዛቢዎቹ እንደነበሩ የገለጹት ዋና አስተባባሪው፣ ፓርቲው የተናገረው ከእውነት የራቀ መሆኑን አክለዋል። ሌላው ሱልካ በተባለ ጣቢያ አካባቢ የፓርቲው ታዛቢ ባጅ ስለተጠየቀ አኩርፎ ከመውጣቱ ውጭ ሌላ የተፈጠረ ነገር እንደሌለም አስረድተዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: