በኢትዮጵያ የመንግስት ስልጣን የሚያዝበት መንገድ “በጦር መሳሪያ ነበር” ሲሉ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ ገለጹ
በኢትዮጵያ የመንግስት ታሪክ ውስጥ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ በአብዛኛው ከጦር መሳሪያ እና በጉልበት የሚመጣ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት በባህርዳር ከተማ በህዳሴ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ተናግረዋል።
ሀገሪቱን ዴሞክራሲን ጀማሪ ብለው የጠሯት ፕሪዝዳንቱ “በእኛ አገር ዴሞክራሲ አለመዳበሩ ብቻ ሳይሆን የመንግስት ስልጣን የሚያዝበት መንገድ ሁላችሁም እንደምታውቁት፣ በታሪካችንም እንደምናውቀው በአብዛኛው በብረት ነው የሚመነጨው፣ ከጦር መሳሪያ ነው የሚመነጨው፣ ከኃይል የሚመነጭ እንጂ ከህዝብ ድምፅ አይመንጭም” በማለት ይህንን የሚያስቀር መንግስታት በህዝብ ድምፅ ብቻ እንዲወጡ የሚያደርግ ነው ሲሉ የምርጫውን አስፈላጊነት አንስተዋል።
በህዝብ እና በዴሞክራሲ የተመረጠ መንግስት መመስረት መልመድ አለብን ሲሉም አክለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚደረግ ምርጫ ሁለት ነገሮችን ያሳካል ብለዋል፡፡ አንዱ መንግስትነት በምርጫ እንጂ በጦርነት እና በአፈሙዝ እንደ ማይገኝ ሲሆን ሌላው ደግሞ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ አሁን ላይ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት የሚፈልጉ አካላት አሉ በማለት በዚህ ሂደት ውስጥ የምታልፍ ከሆነ “ ኢትዮጵያን የጸና መንግስት እና ሥርዓት አይኖራትም” በማለት ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በጸጥታ ስጋት ምክንያት በስምንት የምርጫ ክልሎች ምርጫ የማይደረግ ሲሆን በክልሉ የሚካሄዱት በትጥቅ የታገዙ ግጭቶች መቀጠላቸው በሚዘገብበት ወቅት ነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡(አዲስ ማለዳ)
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.