እንግሊዝ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዜጎቿ የጉዞ ማሳሰቢያ ሰጠች።የብሪታንያ መንግስት ዛሬ ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ ነገ የሚካሄደውን የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
🇪🇹 🇬🇧
እንግሊዝ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዜጎቿ የጉዞ ማሳሰቢያ ሰጠች።
የብሪታንያ መንግስት ዛሬ ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ ነገ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
ማስጠንቀቂያው አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል ለጉዞ አደገኛ አድርጎ በመጥቀስ ዜጎቹ ወደ ትግራይ፣ አማራ እና ጋምቤላ ክልሎች ሙሉ በሙሉ እንዳይጓዙ ከልክሏል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በምትዋሰንባቸው የድንበር አካባቢዎች ከአሥር እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ እንዳይንቀሳቀስ አሳስቧል።
በኦሮሚያ ክልል ከኬንያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር በ10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ፤ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ቄለምም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል ያለው #gov.uk ነው።
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ታደርጋለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: