ከኢትዮጵያ እስከ አውሮፓዊቷ ማድሪድ ከተማ፦ ለሪል እስቴትና ለግንባታ ዘርፍ አዲስ የትብብር ምዕራፍ

- Advertisement -
Sidebar AD

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት፣ የግንባታና የቤት ልማት ዘርፍን በተለያዩ ኢቨንቶች፣ ኤግዚቢሽኖች እና አዋርድ ፕሮግራሞች በማገልገል የሚታወቀው አርኪ ኢቨንት ኦርጋናይዘር፣ ከስፔን ማድሪድ የሚገኘውና የታዋቂውን SIMA Home Expo ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የሪል እስቴት ኢቨንቶችን ከሚያዘጋጀው Planner Exhibitions ጋር ለትብብር ውይይት ወደ ስፔን ሊያቀና ነው።

ግብዣው የቀረበው በኢትዮጵያ በሚካሄደው ኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድ እንዲሁም በቀጣይ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ደረጃ የግንባታና የቤት ልማት ዘርፍን የሚያበረታቱ ፕሮጀክቶችን፣ ኮንፈረንሶችን፣ ኤግዚቢሽኖችን እና የእውቀት ልውውጥ መድረኮችን በጋራ ለማስፋፋት በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ ለመመካከር ነው።

አርኪ ኢቨንት ኦርጋናይዘርም ይህንን ግብዣ ከተቋማዊ ትብብር በላይ፣ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ የሪል እስቴትና የግንባታ ዘርፍ አዳዲስ ዕድሎችን የሚከፍት አጋጣሚ በመሆኑ በበጎ መንፈስ ተቀብሎታል።

በተጨማሪም መንግስት የከፈተውን የሪል እስቴት የኢንቨስትመንት እድል በመጠቀም አውሮፓውያን የሪል እስቴት ኢንቨስተሮችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ እና ከአገር ውስጥ ተዋናዮች ጋር የሚያገናኙ የትብብር መድረኮችን ለመፍጠርም ውይይቶች ይደረጋሉ።

ይህ ውይይት በቀጣይ የአለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ትስስሮችን ለማጠናከር፣ የኢትዮጵያን የሪል እስቴት ገበያ ለዓለም አቀፍ ተዋናዮች ለማስተዋወቅ እና በአፍሪካ የቤት ልማት ዘርፍ ዘላቂ እድገትን ለማበረታታት ጠቃሚ መሠረት ይጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
@planner exhibitions@Arkievent organizers


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: