የሞሮኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ስኬት ታይቶበታል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሞሮኮ ራባት በተካሄደው ሶስተኛው የዳይመንድ ሊግ የራንዌይ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ከፍተኛ ድል እና አንጸባራቂ ውጤት አስመዝግበዋል።

በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፣ አትሌት ሐረገወይን ካልአዩ ደግሞ በ3 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ከ28 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የሀገራቸውን የበላይነት በጋራ አስጠብቀዋል።

በተጨማሪም በሴቶች የ800 ሜትር ፉክክር አትሌት ፅጌ ድጉማ በ1 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ24 ማይክሮ ሰከንድ ፈጣን ጊዜ ሁለተኛ በመሆን አበረታች ውጤት ያስመዘገበች ሲሆን፣ አትሌት ንግስት ጌታቸው ደግሞ በ1 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ 11ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ላይ የተሳተፈው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው የራሱን የዓመቱን ምርጥ ሰዓት በ8 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ በማሻሻል ውድድሩን በ12ኛነት ፈጽሟል።

#athletics #diamondleague #rabat #running #sport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: