ስለ ኒኮሎ ማኪያቬሊ የፖለቲካ ፍልስፍና እና ተፅዕኖ አጭር ቅኝት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታዋቂው አሳቢ ኒኮሎ ማኪያቬሊ እኤአ በ1469 በጣሊያን ፍሎረንስ ከተማ ተወልዶ በ1527 ዓመተ ምህረት አርፏል። ይህ ግለሰብ በዓለም የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እጅግ አወዛጋቢ የሚባል ዘ ፕሪንስ የተሰኘ አነስተኛ መጽሐፍ ደርሷል።

ከእሱ በፊት በርካታ የፖለቲካ ፅንሰ ሀሳቦች የነበሩ ቢሆንም የማኪያቬሊን እይታ ልዩ የሚያደርገው ፖለቲካን ከሥነ ምግባር ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣቱ ነው። እሱ እንደሚያምነው ሥነ ምግባር የማይጨበጥና በስንዝር የማይለካ ረቂቅ ነገር ነው።

ይህ መጽሐፍ ካካተታቸው ዋና ዋና መርሆዎች መካከል መሪዎች ለመፈራትና ለመወደድ መጣር እንዳለባቸው የሚገልጸው ይገኝበታል። ነገር ግን ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ካስፈለገ መፈራትን መምረጥ የተሻለ እንደሆነ ይመክራል።

በተጨማሪም መሪዎች ደካማ ተቃዋሚን መታገስ አለባቸው ይላል። ምክንያቱም ግርግር በሚነሳበት ወቅት ይህንን ደካማ ወገን በቀላሉ በመደምሰስ ለቀሪው ማኅበረሰብ የማያሻማ ማስጠንቀቂያ መስጠት ስለሚያስችል ነው።

ሁለት ወገኖች ሲጋጩም መሪዎች ምንጊዜም ጠንካራውን ወገን መደገፍ እንዳለባቸው ያስገነዝባል። ከግጭቱ በኋላ ድሉ የጠንካራው ስለሚሆን የደካማው ወገን ጥላቻ የሚያመጣው ለውጥ የለም።

በአንጻሩ ሁለቱንም አለመደገፍ የደካማውን ቅያሜ ከማስከተሉም በላይ በጠንካራው ወገን ጥቃት ውስጥ ስለሚጥል እጥፍ ኪሳራን ያስከትላል።

በእኛና መሰል ሀገራት ባሉ የፖለቲካ መሪዎች ዘንድ የሚንጸባረቀው ማኪያቬሊኒዝም የተባለው አስተሳሰብ ከ500 ዓመታት በፊት የተነደፈ ቢሆንም አሁንም ድረስ ይሠራል።

ይህ ፍልስፍና ሥልጣንና መንግሥትን ለማስጠበቅ ሲባል አስፈላጊ ሆኖ የተገኘውን የጭካኔ እርምጃ ሁሉ መውሰድን የሚደግፍና ሌሎች ኃይሎች በርትተው እንዳይነሱ በጥንቃቄ መጠበቅን የሚያዝ በመሆኑ ዲሞክራሲን በእጅጉ ይገዳደራል።

በአጭሩ ሲቀመጥ መድረሻው አካሄዱን ያጸድቀዋል የሚል ይዘት አለው። አሁን ባለው የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ይህንን አስተሳሰብ የሚያራምዱ መሪዎች ሊሳካላቸው ይችላል ወይ የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ነው።

#ማኪያቬሊ #ፖለቲካ #ፍልስፍና #መጽሐፍ #ታሪክ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2