ምርጫ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ተወስኗል

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቡርጂ የምርጫ ጣቢያ ተፈጽሟል በተባለ ሕገ-ወጥ ድርጊት ምክንያት፣ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ መወሰኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ አስታወቁ።

የቦርዱ ሰብሳቢ እንደገለጹት “በቡርጂ ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች እራሳቸው በምርጫ ጣቢያ በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ ምልክት እያደረጉ ድምጽ ሲሰጡ ስለተገኙ ያ ምርጫ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ቦርዱ ወስኖ ዘግቷል። ይሄን ድርጊት የፈጸሙ አስፈጻሚዎች ላይ በቀጣይ የሚወሰደውን እርምጃ በቀጣይ ያሳውቃል” ብለዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: