ሰሞኑን ንግድ ባንክ መመላለስ የስራ ቦታዬ ነው የሚመስለው፣ በዲጂታል ዘመን ንግድ ባንክ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በማላውቀው ተደጋጋሚ እያመላለሰኝ ነው።
በኦላይን ያያዘኩትን ፋይዳ በድንገት አልተያያዘም ብሎ ረጅም ሰልፍ አሰልፎ ከፈተልኝ አሁን ደግሞ ቅዳሜ በድንገት አፕሊኬሽኑ ስራ አቁሞ ድጋሜ ወደ አሰልቺው ቅርጫፍ መስሪያ ቤት ብሄድም ገበያ መስሏል የህዝቡ ብዛት… ጉዳዬን አስረድቼ ለአይፎን ከሰዓት ና አሁን ሲስተም እየሰራ አይደለም ብለው ሸኙን።
እሁድ እና ሰኞን አሳልፌ ዛሬ ወደ ሌላኛው ቅርጫፍ ስሄድ እንደተለመደው በህዝብ ተጨናንቋል በዛ ላይ ሲስተም የለም OTP እያለከ አይደለም ብለው ሸኙን።
ባንኩ ለምንድነው በዚህ ዲጅታል ዘመን ህዝቡን በቅርጫፉ የሚያከማቸው፣ ለምንስ ነው የባንኩ አፕሊኬሽኖች ያለ ምክንያት ስራ የሚያቆሙት?
Source: FastMereja









No comments yet.