በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ ሹመቶች አፀደቀ
ከጦርነቱ በፊት ተቃቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕወሃት ያቀረባቸውን የአዲስ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት ዛሬ ማምሻውን አጸደቀ።
የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ኾነው እንደተሾሙ የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
70 በመቶ ያህሉ የካቢኔ አባላት ከሕወሃት የተውጣጡ ሲሆኑ፣ 30 በመቶዎቹ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምሁራን የተውጣጡ እንደሆኑ ተገልጧል።
በተመሳሳይ፣ ወልደአብርሃ ገብረጻዲቅ የሰሜን ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ሺሻይ ግርማይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ዝናቡ ገብረመድኅን የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ግዴይ አዘናው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ፍስሃ ኃይላይ የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ከለሊ ሐጋዚ የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኾነው እንደተሾሙ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።
@Seledadotio

No comments yet.