ካናዳ : አንጋፋዋ ዘማሪት አዲስ ለማ የዝማሬ አልበም አስመረቀች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታዋቂዋ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ዘማሪት አዲስ ለማ በአዲስ አበባ ብሔራዊ ቴአትር ጀርባ በሚገኘው ታላቁ የቅዱስ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ቤተክርስቲያን ውስጥ በአገልግሎት ያደገች ሲሆን ይህ ደብር በርካታ ታዋቂ ዘማርያንን በማፍራት የሚታወቅ ታሪካዊ ቦታ ነው።

ዘማሪት አዲስ ወደ ውጭ ሀገር ከመጓዟ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ በነበራት ሰፊ አገልግሎት ከፍተኛ አክብሮትን ያተረፈች ሲሆን በተለይም ለምኝ ድንግል ለምኝ፣ በመከራ ፅና፣ ምድረ ቀራንዮ እና ተነሺ ኢትዮጵያ የተሰኙት ዝማሬዎቿ ሁልጊዜ በምእመናን ልብ ውስጥ የሚታወሱ ተወዳጅ ሥራዎቿ ናቸው።

ከሀገር ወጥታ በደቡብ አፍሪካ በኩል አድርጋ በምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት አገልግሎቷን የቀጠለችው ዘማሪት አዲስ ለማ፣ በቅርቡ ካጋጠማት አስከፊ የመኪና አደጋ በተአምር ተርፋ ዛሬ ላይ አዲስ የዝማሬ አልበሟን በበርካታ ወንድሞችና እህቶች ታጅባ በደማቅ ሁኔታ አስመርቃለች።

በአገልግሎቷ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በደግነቷ የምትታወቀው ዘማሪት አዲስ፣ ከዚህ አዲስ አልበም ምርቃት የሚገኘውን ገቢ ሙሉ በሙሉ በካናዳ ካልጋሪ ለሚገኘው የደብረ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ግዢ እንዲሆን በስጦታ አበርክታለች።

ይህ በጎ ተግባር በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን ለአገልጋይዋም መልካም ምኞቶች እየቀረቡላት ይገኛል።

#mezmur #orthodox #ethiopianorthodox #canada #calgary #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: