የአርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ድል በአዲስ አበባ “WE CHAMPIONS 2026” ታሪካዊ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja | አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ ያነሳውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለማክበር ግንቦት 29/2018 በአዲስ አበባ ስታዲየም ታሪካዊ የእግር ኳስና የመዝናኛ ፌስቲቫል ይካሄዳል። በቫርደስ ኢንተርቴይመንት የተዘጋጀውና በአዋሽ ባንክ (አዋሽብር ፕሮ) ዋና ስፖንሰርነት የሚከናወነው ይህ ዝግጅት፣ ከ30 ሺህ በላይ ታዳሚዎችን እና ዓለም አቀፍ እንግዶችን በአንድ ላይ ያሰባስባል።

​ዝግጅቱ የክለቡን ድል ከመዘከር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ አቅሟን ለዓለም የምታሳይበት መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል። በስፍራውም ታዋቂ ድምፃውያን እና የስፖርት ቤተሰቦች ይታደማሉ።

በክስተቱ ላይ የቀድሞው የአርሰናል እና የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቡዌ በልዩ እንግድነት ይገኛል። ከእርሱ በተጨማሪ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ካላቸው የእግር ኳስ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው AFTV ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል። በቡድኑ ውስጥ፡

​ሊ ዳጅስ (Lee Judges) – አቅራቢ (ዩናይትድ ኪንግደም)

​ሴሲል ጂ ቶማስ (Cecil Jee Thomas) – አቅራቢ (ዩናይትድ ኪንግደም)

​ጀረሚ (Jeremy) – ዲጂታል ይዘት ፈጣሪ (ደቡብ አፍሪካ) ይገኙበታል።
በዚህ ዝግጀት ላይ ከ 10 በላይ የሆኑ እውቅ እና ወጣት ኢትዮጵያዊ ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራቸው እንደሚያቀረቡ ተገልጾ ከነዚህም መካከል ታደለ ሮባ ፣ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) ፣ ሳሚ ዳን ፣ አስጌ ዴንዳሾ ፣ ራሄል ጌቱ ፣ ሮቤል ሚዲቅሳ ፣ ዮ ማሪዮስ ፣ ሚክ ዋን ፣ አማኑኤል የማነ ፣ አዲስ ሙላት እንዲሁም እውቁ የዳስሆል/የአፍሮቢትስ ሙዚቃ ተጫዋቹ ፍራንኪዬ ዲ እና ሌሎችም ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ::
የዝግጅቱ ብቸኛ የትኬት መሸጫ መድረክ “አዋሽብር ፕሮ” ነው። ደጋፊዎች ትኬታቸውን በሚከተሉት መንገዶች ማግኘት ይችላሉ፦

​በአዋሽብር ፕሮ አፕሊኬሽን
​በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች (ከ1,000 በላይ ቅርንጫፎች)
​በአዋሽ ብር ፕሮ ኤጀንቶች
​በአዲስ አበባ ስታዲየም በተዘጋጁ ጊዜያዊ መሸጫ ጣቢያዎች (ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 29)

​ከግዢው ጋር በተያያዘ፣ ትኬታቸውን በቅድሚያ ለሚገዙ ደጋፊዎች የ”WE CHAMPIONS 2026″ ይፋዊ ማሊያ የማግኘት ዕድል ተመቻችቷል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: