በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ስርጭት በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ስርጭት
በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዮት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቀናት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል።
እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ያመላክታል።
የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም አስታውቋል።
በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖርም አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።
በሌላ በኩል በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ ይሆናል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: