#Ethiopia | ከ50 በላይ የልብ ሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎችን የያዘ የሕክምና ቡድን ከአንድ ወር በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ተነግሯል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት አራት መሰል ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ያደረገው ‘ኸርት አታክ ኢትዮጵያ’ የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት፤ በቀጣዩ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ቡድን የልብ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ እየተጠባበቁ ለሚገኙ ሕጻናት እና አዋቂዎችን ሕክምና እንደሚሰጥ ገልጿል።
የሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎች ቡድኑ የልብ ስፔሻሊስት ሃኪሞች እና ነርሶች፣ እንዲሁም ሌሎች ባለሞያዎችን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል። የሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎቹ ከህንድ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ሩዋንዳ እና ቦትስዋና የተወጣጡ መሆናቸውንም የኸርት አታክ ኢትዮጵያ መሥራች ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ ገልጸዋል።
ኸርት አታክ ኢትዮጵያ በየጊዜው ተመሳሳይ ሥራዎችን በማከናወን የልብ ሕመም ህክምና ለማግኘት ወረፋ እየተጠባበቁ ለሚገኙ ሕጻናት ሕክምና መስጠቱን እንደሚቀጥልም ዶክተር ተስፋዬ አረጋግጠዋል ሲል ሀገሬ ቴሌቪዥን ነው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#digitalhagerie #Dr.Tesfaye #HeartAttackEthiopia
Source: GetuTemesgen









No comments yet.