የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአርሲ በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ግድያና ቃጠሎ አወገዘ

- Advertisement -
Sidebar AD

​ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአርሲ ዞን አሰኮ፣ ሽርካ፣ ሆንቆሎ፣ ዋቤ እና ሙኔሳ ወረዳዎች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ምዕመናን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ እና የአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ በጽኑ ማውገዙን አስታወቀ።

ጉባኤው በጥቃቱ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጾ፣ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።
​ቀደም ሲል ተመሳሳይ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ጥበቃ እንዲደረግ መጠየቁን ያስታወሰው ጉባኤው፣ አሁንም ችግሩ ባለመቀረፉ ተጨማሪ ጉዳት መድረሱ ሃዘኑን እጥፍ ድርብ እንዳደረገው ገልጿል።

​በመሆኑም መንግሥት የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ተቀዳሚ ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣ ለተፈናቀሉና ስጋት ላለባቸው ዜጎች አስተማማኝ ጥበቃ እንዲያደርግ እንዲሁም ወንጀለኞችን በአፋጣኝ ለፍርድ እንዲያቀርብ በጥብቅ አሳስቧል።

አባል ተቋማት ድርጊቱን በአንድነት እንዲያወግዙና የአካባቢው ማህበረሰብም በጋራ እንዲተጋገዝ ጥሪ አቅርቧል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2