#Ethiopia | አሜሪካ የአፍሪካ አገራትን ጨምሮ በ60 የንግድ አጋሮቿ ላይ ከ10 እስከ 25 በመቶ የሚደርስ አዲስ የጉልበት ብዝበዛ መከላከያ ታሪፍ መጣሏን አስታወቀች።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከዚህ ቀደም ጥሎት የነበረውን ተመሳሳይ ዕገዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ካደረገበት በኋላ፣ አዳዲስ ታሪፎችን ሲያስተላልፍ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
በታሪፉ ከተመቱት 60 አገራት መካከል እንደ ብሪታንያ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ ካናዳ፣ ሕንድ፣ ጃፓን እና ቻይና ያሉ ታላላቅ የምጣኔ ሀብት ኃይሎች የሚገኙበት ሲሆን፣ ከአፍሪካ ደግሞ ደቡብ አፍሪካና ናይጄሪያ በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል።
ውሳኔው የተላለፈው የአሜሪካ ንግድ መሥሪያ ቤት ባለፈው መጋቢት ወር በነዚህ አገራት ላይ የጀመረውን ምርመራ ተከትሎ ሲሆን፣ ተቋሙ አገራቱ የጉልበት ብዝበዛን ለመከላከልና በብዝበዛ የተመረቱ ቁሳቁሶች ወደ ገበያ እንዳይገቡ ለማድረግ የሚያስችል ሕጋዊ ክልከላ አላደረጉም ሲል ከሷል።
ይህ አዲስ ታሪፍ የተጣለው አገራቱ ወደ አሜሪካ በሚልኳቸው “በሁሉም ቁሳቁሶች” ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#USA #TradeTariff #DonaldTrump #GlobalEconomy #LabourExploitation #Africa #EconomicNews
Source: GetuTemesgen









No comments yet.