ለኮሪደር ልማት አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ የሰረቀ ግለሰብ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተያዘ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በረከት አረጋ የተባለ ግለሰብ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ጉስቋም ቅድስት ማርያም አካባቢ ከምሽቱ 4:00 ሠዓት ላይ ነው።

ተጠርጣሪው በሠዓቱ ለኮሪደር ልማት ተዘርግቶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብል በመጋዝ ቆርጦ በመውሰድ በውሃ ፍሳሽ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ገብቶ ለመሰወር ቢሞክርም በወቅቱ ስራ የነበሩ የፖሊስ አባላት ተከትለው በመግባት ሁለት ሰአት በፈጀ ፍለጋ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጦር ስር በማዋል አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ገልጿል ።

ወንጀል ፈፃሚው በወቅቱ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ትብብር ማድረጉ የሚያስመሰግን ተግባር ነው ያለው ፖሊስ ህዝብ ሲተባበር ወንጀል ፈጻሚዎችን በቀላሉ ለህግ ማቅረብ እንደሚቻልም አመላክቷል ብሏል።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያም ከአስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የፍሳሽ መውረጃ ትቦ ውስጥ ገብተው ተጠርጣሪውን ለያዙት አባላት ማበረታቻና ሽልማት እንደሚሰጥም አሳውቋል።

አዲስ አበባ ፖሊስ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2