🙏
አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው!!!
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ “እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” በማለት ትንቢት እንደተናገረው የተስፋው ቃል ይፈጸም ዘንድ በዘመነ ሥጋዌ እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወለደ፡፡ በኢሳይያስ 7÷14፣ በማቴዎስ 1÷23 እንደተጻፈው መልአኩ የመውለዷን ነገር “እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ስሙንም አማኑኤል ትይለዋለች፤ አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።” ሲል አበሠራት፡፡ ሰዎች በሕይወት ዘመናችን ችግርና መከራ ሲጸናብንና ፈተናችን ሲበዛ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሆነ ማሰብ ያዳግተናል፤ እንዲያውም ጨርሶ እንደተወንም እናስባለን፡፡ ሆኖም ግን ፈጣሪያችን ሁሉን የሚያደርገው በምክንያት በመሆኑ ፈተናችን ለበጎ እንደሆነ በማሰብ ጸንተን መጓዝ ያስፈልጋል፡፡ እርሱ ሁሌም ከእኛ ጋር ነውና፡፡
አማኑኤል ‹አማነ› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፤ ትርጓሜውም የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ደግሞ ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ የተዋሐደ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር እንደኛ የሆነ ማለት ነው። አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሞት ፍርድ በተፈረደበት ጊዜ አምላኩ እግዚአብሔር እዲያድነው ስለተማጸነው በርኅራኄው ወደ ቀድሞ ቦታው እንደሚመልሰው በሰጠው ተስፋ ከልጅ ልጁ ተወለዶ አዳነው፡፡ በዚያችም በተከበረች ቀን ትንቢቱ ተፍጽሞ አምላካችን ከእኛ ጋር ሆነ፡፡ አምላክ ሰው የሆነለት የሰው ልጅ ኃጢአት ተፋቀ፡፡ ስለዚህ ከኃጢአት ርቀን በስሙ ተቀድስን እንድኖር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ የሰው ልጅ ሕይወት ይቀደሳል ማለት ነው፡፡
አንድም “ዒማኑ” ማለት ምስሌነ ከእኛ ጋር ማለት ሲሆን፣ “ኤል” አምላክ የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ በጥቅሉም “አምላክ ምስሌነ፣ ወይም ምስሌነ አምላክ፣” አምላክ ከኛ ጋራ ማለት መሆኑ በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌልና በትንቢተ ኢሳይያስ መገለጹን ከላይ አይተናል፡፡ ሊቃውንት ግን “አምላክ ወሰብእ” “አምላክም ሰውም” ወይም ሰው የሆነ አምላክ፣ በመለኮቱ አምላክ፣ በለበሰው ስጋም ሰው ብለው በምስጢር አፈታት ይፈቱታል፡፡ አንድም ዐማኑኤል “ወዝስም ዘውእቱ ዐማኑኤል ዐቢይ ጥቀ ወኢደሉ ፈሊጦቱ ወውእቱ ዘበአማን ምስጢር ለጽንዐ ሃይማኖት” “ይህ ዐማኑኤል የተባለ ስም እጅግ ታላቅ ስም ነው፣ የማይለይ ተዋሕዶን የሚገልጽ የሃይማኖት መሠረት ነው” ይሉናል፡፡ ይህን ስም ተመክተው ነው ገዳማውያኑ ዓለምን ንቀው የመነኑት፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Source: Yeneta Tube









No comments yet.