እዳ ባለመከፈሉ ኢትዮጵያ ልትከሰስ#የኢትዮጵያ #ዩሮቦንድ አበዳሪዎች ያልተከፈለ ዕዳን በተመለከተ መንግሥትን ለመክሰስ የሕግ ሂደ…

- Advertisement -
Sidebar AD
እዳ ባለመከፈሉ ኢትዮጵያ ልትከሰስ‼️
#የኢትዮጵያ #ዩሮቦንድ አበዳሪዎች ያልተከፈለ ዕዳን በተመለከተ መንግሥትን ለመክሰስ የሕግ ሂደት መጀመራቸው ተዘገበ‼️
የኢትዮጵያ የዩሮቦንድ አበዳሪዎች ቡድን፣ መንግሥት ያልከፈለውን የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በተመለከተ ክስ ለመመሥረት የሚያስችላቸውን የሕግ ሂደት በይፋ መጀመራቸው ተዘገበ።
ብሉምበርግ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ ‘አድ ሆክ’ የቦንድ ባለቤቶች ኮሚቴ (Ethiopia Ad Hoc Bondholder Committee) አባላት፣ በእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ክስ ለመመሥረት ማቀዳቸውን የሚገልጽ የቅድመ-ክስ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ባለፈው ሳምንት ለኢትዮጵያ መንግሥት ልከዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት፣ መንግሥት ደብዳቤው እንደደረሰው ለማሳወቅ 14 ቀናት አሉት ያሉ ሲሆን፣ ሆኖም የጊዜ ገደቡ መቼ እንደሚጀምር በዝርዝር አላብራሩም።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: