ኦብነግ ከፋኖ ጋር መነጋገሩን ይፋ አደረገከአንድ ወር በፊት በአስመራ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተገናኙት የኦብነግ አንጃ መሪ የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኦብነግ ከፋኖ ጋር መነጋገሩን ይፋ አደረገ
ከአንድ ወር በፊት በአስመራ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተገናኙት የኦብነግ አንጃ መሪ የሆኑት አብዱራህማን መህዲ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ንግግር እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ትናንት ባወጣው ዘገባ፣ ከሰላማዊ ትግል ራሱን ያገለለው የኦብነግ አንጃ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ እና አማጺ ኃይሎች ጋር ጥምረት እንዲፈጥሩ ከግብጽ እና ኤርትራ መንግስታት ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች በጋራ እየተሰባሰቡ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው፤ ከሚሰባሰቡት ኃይሎች መካከል ኦብነግ አንዱ ነው ብሏል፡፡ እንደ ፋኖ፣ ህውሃት እና ኦነግ ሸኔ ካሉ ሀይሎች ጋር ጥምረት መፍጠራቸውን በአፍሪካ ኢንተለጀንስ የተጠየቁት የቡድኑ መሪ አብዱራህማን መህዲ፤ ‹‹ጥምረት የመፍጠር ደረጃ ላይ ባንደርስም፤ ከፋኖም ሆነ ሌሎች ሀይሎች ጋር ተነጋግረናል፤ ለመስራትም ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን ውይጥቱ የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም›› በማለት መልሰዋል፡፡
አፍሪካን ኢንተለጀንስ እንደዘገባው፣ የኦብነግ አንጃ ከሌሎች ሀይሎች ጋር ትብብር እንዲፈጥር፣ በሱዳን፣ ኤርትራ እና ግብጽ መንግስታት ጫና እየተደረገበት ሲሆን፤ በቅርቡም በአስመራ እና በፖርት ሱዳን ስብሰባዎችን ማደረረጋቸውን ጠቅሷል፡፡via:- andafta
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: