የመርሐግብር ለውጥ

- Advertisement -
Sidebar AD

ከግንቦት 29 እና 30 ወደ ሰኔ 5 እና 6 ተዛውሯል

ከሕንፃ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ሥላሴ ይቀድማል

እኛ የወሎ መርሣ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እናቶች እና አባቶች እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች በውኃ ጥም እየተሰቃዬን እንገኛለን። ለዚህም ከገጠር መጥተን አዲስ አበባ ከተቀመጥን ሳምንት አለፈን።

አመጣጣችንም ግንቦት 29 እና 30/2018 የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እና የእራት መርሐግብር አድርገን ለገዳሙ የውኃ ፕሮጀክት 10,000,000 /ዐሥር ሚሊዬን ብር ለማሰባሰብ ነበር። ነገር ግን የአርሲው ጭፍጨፋ በወገኖቻችን እና በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጸመ። እኛም ልባችን ተሠበረ። እንዴት በዚህ ሰዓት እራት እና ቀጥታ ሥርጭት እያልን እንለምናለን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት እናራዝመው ብለን ወደ ሰኔ 5 እና 7 አርብ እና ቅዳሜ አሸጋግረነዋል።

ይኽን ስናደርግ እኛ ከገዳም የመጣን መነኮሳት ከሰው ቤት ለ15 ቀናት እንደምንቀመጥ ስናስብ በሁለት ነገር እናዝናለን። አንደኛ ከተማ መቀመጥ ለኛ አይገባም። ሁለተኛ ማረፊያ ለሰጡን ወገኖች ሸክም እንሆናለን።

ይኹንና ከገጠመን ኅዘን የሚበልጥ ነገር ስለሌለ አዛውረነዋል። እናንተም ሰኔ 5 እና 6
ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እየገባችሁ ልጆቻችን አለን በሉን።

አደራ ልጆቻችን
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ደውሉልን
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: