የ17 ዓመት ሴት ልጅ ጅብ ልበለኝ ነው ክፈችልኝ በር ብሎ በማታለል ወደ ቤት በመግባት ክብረ ንጽሕና የገረሰሰው ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
1ኛ ተካሳሽ አቶ ከፍያለሁ ደሳለኝ ኦቤ የተባለው በይርጋጨፌ ወረዳ ጭቶ ቀበሌ ልዩ ሰፍራ ሸፈሮ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ላይ ከምሽቱ 6:00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በራሷ ቤት ተኝታ ባለችበት ቤቱን ጅብ በለኝ ክፈችልኝ ብሎ ስለምናት ስትከፍትለት በጉልቤት በጉልበት አሳምኖና ሀይል ተጠቅሞ እሰከ ንጋቱ ደረሰ በተደጋጋሚ የግብሬ ስጋ ግኙንነትና የኃይል ድርግት በመጠቀም ያለ ፍላጎታ አሰቦና አቅዶ በፈፀመ አስገድዶ የመድፈር ወንጄል ክስ ቀርባል
2ኛ ተከሳሽ አቶ መስፍን ለማ ገመዴ በይርጋጨፌ ወረዳ አርቻ ቀበሌ ልዩ ስፍራ ቦትቆ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ከምሽቱ 1:30 በሚሆንቤት ጊዜ ላይ ተከሳሹ በመንገድ ላይ ጠብቆ ሳትፈልግ በጉሉበት በማሳ ወስጥ ጎትቶ በመዉሰድ የለበሰችን ፓንት ቀዳዶ በኃይል ሳትፈልግ አስገድዶ በመድፈር ክብረ ንፅናዋን ገርስሰዋል በሚል ክስ ቀርባዋል
በሁለቱም ተከሳሾች የቀረበውን ክስ በሰውና በሰነድ ማስራጃ ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ መዝገቡን ለወረዳ ዐቃቤ ህግ ማስተላሌፋቸውን የገለፁት የወረዳ ፖሊስ መርማር ምክትል ኩማንደር ውሌታ ሞኮንን ናቸው
የይርጋጨፌ ወረዳ ዐቃቤ ህግ የሆኑት አቶ አብነት ጌታቸው ፖሊስ አጣርቶ የላከውን መዝገብ በተከሳሾች ላይ በ1997 ዓ.ም በሥራ ላይ በዋለው በኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀፅ 620 (1) ስሪ የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፋቸው በሚል በተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ህግ ክሱን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
በዚህ መነሻነት በተከሳሾች ላይ ክስ ተመሰረተው በቀን 27/09/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ማንነት ካረጋገጠ በኃላ ተከሳሾች የወንጀሉን ድርግት አልፈፀምንም ፡ ጥፋተኞች አይደለንም ብሎው ክደው በመከራከራቸው የይርጋጨፌ ወረዳ ዐቃቤ ህግ አለኝ ያለውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለፍ/ቤቱ አቅርበው ጉዳዮን እያከራከረ ቆይተው ዛሬ ግንቦት 27/9/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾችሁን ያርማል ለሎችንም ያስተምራል በማለት ፍርድ ቤቱ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ከፍያለሁ ደሳለኝ 6 ዓመት እስራት እንድቀጣ 2ኛ አቶ መሰፍን ለማ 7 ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ፍ/ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።
ዘገባ፦ የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት
ረ/ኢ/ር ጌቱ ሲሳይ

Source: Yeneta Tube









No comments yet.