#Ethiopia | በጣሊያን መዲና ሮም ነዋሪ የሆኑት ሎሬንዞ ቦሲ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩት አባታቸው ኤንሪኮ ቦሲ የወረሷቸውን 18 ታሪካዊ የኢትዮጵያ የእጅ ሥራ መስቀሎች በሮም ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረክበዋል።
አባታቸው ኤንሪኮ ቦሲ በሕይወት በነበሩበት ወቅት የኢትዮጵያን ጥንታዊ ቅርሶች በመሰብሰብና ስለ አገሪቱ ታሪክ ከሃያ በላይ መጻሕፍትን በማተም የሚታወቁ ባለውለታ ነበሩ።
በጣሊያን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ እነዚህን ውድ ቅርሶች በይፋ ላስረከቡት ሎሬንዞ ቦሲ የላቀ ምስጋናቸውን በመግለጽ የክብር ምስክር ወረቀት ሰጥተዋቸዋል።
በሮም የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አባላትና የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት የተከናወነው ይህ ታሪካዊ ርክክብ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ቅርሶቹ ከሮም ወደ አገር ቤት የሚመለሱበትን የጉዞ ሂደት ከኤምባሲው ጋር በመተባበር እያመቻቸ መሆኑን ገልጿል።
#EthiopianHeritage #HistoryRestored #AfricanArtifacts #BringBackOurHeritage #EthiopianHistory #CulturalRestitution #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.