“ወ/ሮ በረከት ወርቁን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ለችሎት እንዲቀርቡ የጋዜጣ ጥሪ እንዲወጣ ታዘዘ።”ፖሊስ የሙስና ወንጀል ተከሰው በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
“ወ/ሮ በረከት ወርቁን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ለችሎት እንዲቀርቡ የጋዜጣ ጥሪ እንዲወጣ ታዘዘ።”
ፖሊስ የሙስና ወንጀል ተከሰው በፖሊስ የፍለጋ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱትን ወ/ሮ በረከት ወርቁን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን ፖሊስ ለፍርድ ቤት ማቅረብ አልቻለም።
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ በ13 ተከሳሾች ላይ የተመሰረተውን ክስ መርምሯል።
በዚህ መዝገብ ውስጥ የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎችም ተካተዋል።
አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ ስልጣናቸውን ከህግ ውጭ በመጠቀምና የመንግስት ሥራን ተገቢ ባልሆነ መንገድ በመምራት ጉዳት አድርሰዋል በሚል ክስ አቅርቧል።
ለዛሬ ተይዞ በነበረው ችሎት ከ6ኛ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር የተመዘገቡ ተከሳሾች ባለመገኘታቸው ሂደቱ ተራዝሟል። ፍርድ ቤቱም እነዚህ ግለሰቦች በጋዜጣ ጥሪ እንዲጠሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በተለይ ወ/ሮ በረከት ወርቁ ከሀገር ውጭ መገኘታቸው በማህበራዊ ሚዲያ በሚታዩ መረጃዎች መጠቆሙን ተከትሎ፣ ጥሪው በአዲስ ዘመን እና በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጦች እንዲታተም ተወስኗል።
ችሎቱ አቃቤ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በማዘዝ፣ የጉዳዩን ቀጣይ ሂደት ለመከታተል ለሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via ሸገር ኤፍኤም
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2