(አዲስ ፖሊስ)፦ ግለሰቦቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ህንፃ ውስጥ ነው።
ዘነበ ንጉሴ የተባለው ግለሠብ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ የህንፃ መጠቀሚያ ባለሙያ ሲሆን የግል ተበዳይ የግንባታ ፍቃድ ለማውጣት 100ሺ ብር ተጠይቀው በድርድር 50ሺ ብር ይዘው እንዲመጡ ተስማምተዋል።
የግል ተበዳይ የደረሰባቸውን በደል ለክፍለ ከተማው ፖሊስ የወንጀል መከላከል መምሪያ በሰጡት ጥቆማ ተጠርጣሪው በክትትል አባሎች ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል።
ከጉዳዩ ጋር ተሳትፎ የነበረው በክፍለ ከተማው የግንባታ ፈቃድ የመጠቀሚያ ፈቃድ ባለሙያ የሆነው አድምቀው ውቤ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይን ጉቦ ካልከፈልክ አገልግሎት እንደማይሰጠው በመንገርና ለአንድ ወር በማጉላላት 50ሺ ብሩን እንዲሰጥ በማድረግ የማግባባት ስራ ሲስራ እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።
ህብረተሰቡ መብቱን በገንዘብ መግዛት እንደሌለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሠል የወንጀል ድርጊት ሲፈጸም ጉዳዩን በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (citizen engagement application) በመጠቀም መረጃ መስጠት እንደሚችልም ገልጿል፡፡
Source: FastMereja









No comments yet.