በአገራችን የባንክ ሂሳብ ሊኖራቸው ከሚገባ አዋቂዎች መካከል የባንክ ሂሳብ ያላቸው ከ50 በመቶ በታች ናቸው ተባለ
በ2025 የወጣ የፋይናንሻል ኢንዴክስ ሪፖርት እንዳሳየው በአገራችን የባንክ ሂሳብ ያላቸው አዋቂዎች ቁጥር 49 በመቶ ነው።
በአገራችን በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች የባንክ ሂሳብ የላቸውም ተብሏል።
ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን የማስፋት ንቅናቄ መድረክ ባዘጋጀበት ወቅት ነው።
ከሰኔ 18/2018 እስከ መጋቢት 2019 ዓ.ም የሚቆየው ይህ ንቅናቄ” አካታች የባንክ አገልግሎት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።
ይህ አገልግሎት ከፋይናንስ አገልግሎት ተገልለው ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የተዘጋጀ ነው።
በአፋር ፣ ኦሮሚያ ፣ ሶማሌ፣ አማራ እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚገኙ 2መቶ 41 ወረዳዎች ላይ ይተገበራል።
ከግማሽ ሚሊየን በላይ አዳዲስ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ተደራሽ ለማድረግ ይሰራል ያሉት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ናቸው።
በተያዘው ዕቅድ መሰረት 3መቶ 50 ሺህ የሚሆነው የባንክ ሂሳብ በባንክ በኩል ቀሪው 1መቶ 50 ሺው ደግሞ በሲቢኢ ብር በኩል የሚከፈት ይሆናል።
@Seledadotio

No comments yet.